የLTV
Show አዘጋጅ ቤተልሔም ታፈሰ እና የአ.ብ.ን ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ያደረጉትን ሙግት መሰል ውይይት በጥሞና አዳመጥሁት፡፡
የዐማራው ማኅበረሰብ የሕልውና ፈተና ገጥሞታል የሚለው የንቅናቄው አቋም የተመላለሱት ጉዳይ ግልጽ ሊሆንልኝ አልቻለም፡፡ ጋዜጠኛዋ
ትንኮሳ ትላለች፤ ሊቀ መንበሩ ደግሞ የህልውና ፈተና ይላሉ፡፡ የሕልውና ፈተና መሆኑን ለማስረዳት ብዙ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይችሉ
የነበረ ቢሆንም ረግጦ የማስረዳት ክፍተት አስተውየባቸዋለሁ፡፡ ጋዜጠኛዋም በበኩሏ የሕዝብ ቁጥር ብዛትን እየጠቀሰች ያህን ያህል
ስፋት ያለው ማኅበረሰብ እንዴት የሕልውና ፈተና አለበት ሊባል ይችላል እያለች ትሞግታለች፡፡ ይህ ሁሉ አስፈላጊ ነበር ወይ የሚለው
እንዳለ ሆኖ የሕልውና ፈተና ተጋርጦበታል ለሚለው ጉዳይ የሚከተሉትን አስረጂዎች ማየት ይቻላል፡፡
በዐማራው
ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል ሲባል፡-
1. ዐማራው
በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በጅምላ ሲገደል፣ ቤት ተዘግቶበት ሲቃጠል፣ ሲፋናቀልና ከርስቱ ሲነቀል የቆየ መሆኑ፤
አሁንም እነዚህ ጉዳዮች እየተፈጸሙ መሆናቸው፣
2. የቤተሰብ
ምጣኔን እንደሽፋን የዐማራ ወጣቶች መውለድ እንዳይችሉ የማድረግ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸው፣
3. ወንጀል
ሳይኖርባቸው ዐማራ መሆናቸውና መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ በየማጎሪያ ቤቱ እየሰበሰቡ እንዳይወልድ የማኮላሸት ሥራ እየተሠራበት
መሆኑ፣
4. የመንግሥት
ሥርዓትን ከሚመሩ ድርጅቶች ጀምሮ በሐገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ዐማራን ጠላትና ጨቋኝ አድርጎ የመተረክና ይህንንም
ለማስረጽ በተለያዩ መንገዶች እየተሠራ መሆኑ፣
5. በኢኮኖሚ
ሥርዓቱ ግፉእ እንዲሆን የማድረድ ተግባር በፖሊሲ ደረጃ ተቀርፆ የሚሠራበት መሆኑ፣
6. ዐማራው
በሐገሩ ማግኘት የሚገባውን ማግኘት እንዳይችል፤ ከማይምነት እንዳይላቀቅና በድኅነት ሲማቅቅ እንዲኖር እየተሠራበት መሆኑ፣
7. በተለይም
ጋዜጠኛዋ ራሷ የመከራከሪያ ነጥብ አድርጋ ለማሳመኛነት ያቀረበችው ጉዳይ ዐማራው ምን ያህል የህልውና ፈተና የገጠመው እንደሆነ ለማሳያነት
የሚቀርብ እንጂ እሷ እንዳለችው የሕልውና ፈተና የሌለበት መሆኑን ሊያሳይ የሚችል አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የዐማራውን ያህል
በሥፋትና በከፍተኛ ሁኔታ ተሠራጭቶ የሚኖር ሌላ ማኅበረሰብ የለም፡፡ በየትኛውም የሀገሪቷ አካባቢዎች በጣም በርካታ ቁጥር ያላቸው
አማሮች ይኖራሉ፡፡ በ2010 መስከረም ወር ላይ እን ኦቦ ለማ መገርሳ እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል ብቻ እስከ 11, 000, 000
የሚደርሱ ዐማሮች ይገኛሉ፡፡ በሌሎች አካባቢዎችም ከዚህ የሚበልጥ ቁጥር ያለው ዐማራ አለ፡፡ ይሁን እንጂ በመንግሥት ደረጃ በታቀደና
በታሰበበት መንገድ የዐማራውን ቁጥር የማሳነስ ሥራ ሲሠራ ኖሯል፡፡ ብዛቱ ከሐገሪቱ ሕዝብ እስከ 50% የሚሆነውን የመሚሸፍን ሆኖ
እያለ በቁጥር ሁለተኛ እንደሆነ ፐሮፓጋንዳ መነዛቱ፣ በሕዝብና ቤት ቆጠራ ሪፖርትም የሕዝብ ቁጥሩ እየቀነሰ መሆኑ፣
8. በተለያዩ
የሐገሪቷ አካባቢዎች በሥፋት ተሠራጭቶ የሚኖረው ዐማራ ዐማራ ነኝ ሲል ከመንግሥት ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም የሚያስከለክለው በመሆኑ
ምክንያት፣ ልጆቹ ቢማሩም ባይማሩም የሥራ እድል እናዳያገኙ የሚገደዱ በመሆናቸውም ምክንያት ዐማራነታቸውን ትተው በሌላ ብሔረሰብ
ስም እየተመዘገቡ እንዲኖሩ እየተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
በመሆኑም
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ምክንያቶች ዐማራው የሐገር አልባነት ስሜት እንዲሰማውና ተረጋግቶ ሕይወትን መምራት እንዳይችል የሚያደርጉ፤
በሕይወቱም ተስፈኛ እንዳይሆንና በሐገሩ እየተሳቀቀ እንዲኖር የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ከዚህም በላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ የቁጥር መቀነስን
እያመጡ የአናሳ ናችሁ እኛ ከናንተ የበለጠ ጥቅም ማግኘት ይገባናል የሚሉ ትረክቶች እንዲያቆጠቁጡ እያደረገ ነው፡፡ የሕልውና አደጋ
(ፈተና) ሲባልም ሙሉ ለሙሉ የመውደም ጉዳይ ሳይሆን የነበረን መሠረት የማሳጣት፣ የማኅበረሰብን ሥነ ልቡና የማዳከምና በሐገሩ ጉዳይ
አንገቱን ደፍቶ ሁሌም ተበዝባዥ አድርጎ የማስቀጠል ጉዳይን የሚመለከት ነው፡፡
No comments:
Post a Comment