(የዘፈኑ ‹ሙዚቃው› አጠቃላይ ሁኔታ)
የት ነበር ያኖርኩት ቀፎዬን ስል ኖሬ
ንብ ተከትዬ ባይ ጎጃም ኑራ ማሬ፡፡
ብራናየ አንች የልጅነት ጓዴ
ተረሳሽ ወይ የሳቱ ዳር ተረት ባንዴ::
በዘብህ የተሰደደው ፍቅሩን (ሰብለወንጌል መሸሻን) ጎጃም አስቀምጦ ነው፡፡ ጎጃም ተስፋው
አለች፡፡ ተስፋው ተከትላው መምጣት አልቻለችም፡፡ ትመጣለች ብሎ እየጠበቃት የውኃ ሽታ ሆና ስትቀርበት ፍቆት ሽታውን ሊፈልጋት ተመልሶ
ወደ ጎጃም ጉዞ ጀመረ፡፡ የጎጃምን ምድር ዳርቻውን እንደረገጠ በሽፍቶች ተደብድቦ መራመድ እንኳን አቅቶት መንገድ ላይ ወድቆ አንዲት
ሴት ታገኘውና ታስጠጋዋለች፡፡ በተጠጋበት ቤት ተስፋው ተቆራምዳ፣ መንኩሳ ቢጫ ልብስ ለብሳ ያገኛታል፡፡ በጣዕርና በሳቅ መሐል ሆኖ
ሕይወቱ ታልፋለች፡፡
ይህ ፍቅር እስከመቃብር የተሰኘው ድንቅ መጽሐፍ የሚተርክልን ጉዳይ ነው፡፡ ይሀንን ነገር
ቴዎድሮስ ካሳሁን በሙዚቃ ሰርቶ ሲያመጣልን ፍቅር እስከመቃብር የያዘው አድማስ ብቻ እንዲበቃው ሆኖ የቀረበ ሆኖ አይታየኝም፡፡ ይህንን
እምነቴን ያስረዱልኝ ዘንድ ሁለት ነገሮችን እጠቅሳለሁ (ለጊዜው)፡፡
1. 1. ዜማው፡- ሲጀምር ከቅዳሴ ዜማ
ይነሳና ወደሚያስደልቅ ደማቅ የጎጃም ባሕላዊ ጭፈራ ምት ይሸጋገራል፡፡ ቅዳሴ በጎጃም ማኅበረሰብ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ከገበሬው
እስከ ካህናቱ ቅዳሴ ቢታጎል መዓት የሚወርድባቸው፤ አምላካቸው ወደ ምድር መጥቶ ተሰቃይቶ የሚሞት የሚመስላቸው ናቸው፡፡ ቅዳሴ ከተጀመረ
በኋላ ማንም እንዳይገባ የደጀ ሰላማቸውን በር ግጥም አድርገው ዘግተው በጥሞና የሚከታተሉ፣ በሩ ተከፍቶ ሰው ጥሶ ከገባ አካላቸው
የተረገጠ ያህል ስቅቅ የሚላቸው፣ መላእክት ወደምድር መጥተው ለአምላካቸው እየሰገዱና እያሸበሸቡ እያለ ተረገጡ ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡
ሥለሆነም ዜማው በቅዳሴ መጀመሩ ስራው ማኅበረሰቡን በጥልቀት ከማየትና ከመረዳት የመነጨ መሆኑንና እጅግም በጥንቃቄ የተሠራ መሆኑን
ያሳያል፡፡
ዜማው በቅዳሴ እንጀመረ በዚያው አይቀጥልም፡፡ አንጀት ወደሚበላ ነገር ግን ወደለቅሶ በሚመራ
ደማቅ ዜማ ይሸጋገራል፡፡ ጎጃሞች የሚደልቁት ሲደሰቱ ብቻ አይደለም፤ ሲያዝኑም አንጂ፡፡ ጎጃሞች ሰው ሲሞት በየአድባሮቻቸው አደባባይ
በመገኘት ሙሾ ያወርዳሉ፡፡ ሙሾው እጅግ ግጥም አዋቂነታቸው በተመሰከረላቸው
አስለቃሾች እየተመራ በረገዶ ታጅቦ በእናቶች ደረት ድቂ እየደመቀ የተለየ የሐዘን ስሜትን የሚፈጥር ዜማ ይፈጥራል፡፡
ዜማው እንጉርጉሮም ድለቃ የሚመስል ድምፀትም ያለው ነው፡፡ ይህ ድምፀት ነው በቴዎድሮስ ካሳሁን “ማር እስከ ጧፍ” ሙዚቃ ውስጥ
የሚስተዋለው፡፡
ጎጃሞች በደስታቸው ወቅት መንደራቸው ምድርን በሚያንቀጠቅጥ ድለቃ ይቀልጣል፡፡ አዝመራ
ከመሰብሰብ እስከሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ባለው የእርስበርስ ግንኙነታቸው የደመቀ ጭፈራ ከመንደሮቻቸው አይጠፋም፡፡ ጧፍ ውስጥ የሚገኙት
ቁጢቶች ሰም አስተባብሮ እንዳያያዛቸው ጎጃሞችን አጣምሮ የሚያያይዛቸውና ኑሯቸውን በሕብረት እንዲመሩ የሚያደርጋቸው ፍቅር ነው፡፡
ያ ፍቅራቸው ደግሞ የሚገለጸው ልብን በሚያሞቀው ዜማቸው ነው፡፡ ዜማ የሁሉ ነገራቸው መግለጫ መሣሪያ ነው፡፡ ዓይነቱ ይለያይ ይሆናል
እንጂ፡፡
22. በግጥሙ ውስጥ የሚጠቀሱት ቃላት፡-
በዚህ ሙዚቃ ግጥም ውስጥ ቴዎድሮስ ካሳሁን የተጠቀማቸው ቃላት እጅጉን ለጎጃምና ጎጃሜዎች የቀረቡ ናቸው፡፡ ይህም ከያኒው ሥራውን
ለመሥራት ምን ይህል ስለማኅበረሰቡና ማኅበረሰቡ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ስለተጻፈው ፍቅር እስከመቃብር መጽሐፍ በጽሞና አንዳሰላሰለ
የሚያሳይ ነው፡፡ “የፀበል ዳር እንኮይ ወንዝ ያወዛት ቅጠል” ይላል የዘፈኑ ግጥም ጀመሪያ ስንኝ፡፡ ፀበልና እንኮይ ከጎጃም ማኅበረሰብና
ልጆች ጋር ከፍተኛ ትስስር ያላቸው ናቸው፡፡ ፀበል በጎጃም ማኅበረሰብ ዘንድ እጅግ የተከበረና ከማንኛውም ዓይነት የሕክምና ተግባር
ቅድሚያ የሚሰጠው ፈውስ የማግኛ መንገድ ነው፡፡ እናም ከያኒው ሰብለወንጌልን ለመግለጽ የተጠቀመው፡፡
ኑራ-በተለመደው ዐማርኛ የሆነ ቦታ (ሥፍራ) ቆይታ የሚል ፍቺ አለው፡፡ ሌላ ተጨማሪ ፍቺም ይሸከማል፡፡ አንድም የሆነ ቦታ እያለች (ሳለች) ነው ለካ…
የሚል፤ አንድም ለካ እሷ ናት እንደማለት፡፡ በቴዲ አፍሮ ዘፈን ተደጋግሞ የሚጠራው ቃልም “ጎጃም ኑራ ማሬ” የሚል ነው፡፡ ጎጃም
“ጎጃም ኑራ ማሬ” ሲል አንድም በዛብህን የወከለው ሰው ሰብለ ወንጌልን ሸዋ ሲጠብቃት እሷ ግን ጎጃም ያች መሆኗን አመልካች ነው፡፡
አሊያም የኔ መድኃኒት ጎጃም ነች እንደማለትም አድርገን መውሰድ እንችላለን፡፡
ማር ከጣፋጭነቱ በተጨማሪ መድኃኒትነቱ ፍቱን የሆነ
መሆኑ የታወቀ ሐቅ ነው፡፡ (ይቀጥላል-- ተጠናክሮ)