Monday, January 5, 2015

ብቸኛ

ያምሃል አለኝ ገና እንዳገኘኝ፡፡ ምንም አልመለስኩለትም፡፡ ፊቴን ቅጭም አድርጌ ዐይኖቼን አጥብቤ አየሁት፡፡ ውስጤን ዘልቆ ያየኝ እስኪመስለኝ አፈጠጠብኝ፡፡ ማመምማ አሞሃል፡፡ ጸበል ወይም ሀኪም ቤት መሄድ ነበረብህ ማለት ጀመረ፡፡

አዎ አሞኛል፡፡ በጣም ነው የሚያመኝ፤ ስሟን እየጠራ የሚያስታውሰኝ ሰው በመጣ ቁጥር እታመማለሁ፡፡ ራሴን ነጻ አድርጌ ለመስራት እየጣርኩ ለውጥ ለማምጣት ደፋ ቀና እያልኩ የተሸለ ስራ መስራት እንደጀመርኩ አንዱ ያነሳታል፡፡ ያን ጊዜ የኔ ውስጥ ይናወጣል፡፡ ሁሉም ነገር ያመኛል፡፡ ስራ ያስጠላኛል፡፡ መተኛት ያምረኛል፡፡ እንቅልፍ ይጫጫነኛል፡፡

ስለዚህ በቃ ማንንም መግኘት የለብኝም፤ ሁሉም ሰዎች ጠላቶቼ ናቸው፡፡ የማልፈልገውን ነገር መረዳት እስካልቻሉና እኔን ለህመም እስከዳረጉ ድረስ የሰዎች ወዳጅነት ምኔም አይደለም፡፡ እነሱ ለኔ ጥሩ ከማሰብ እያሰረጉት ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የስሜቴን መለዋወጥ ተመልክተው ሊረዱ ይገባል፡፡ አለበለዚያ የእኔን ህይወት አደጋ ውስጥ የሚከት ማናቸውም ምክርና ሀሳባቸውን ይዘው በዚያው በየትንኩርሽታቸው ….
...
    በአያገባው ነገር በሰው እየገባ
    ውስጡ ባዶ ሲሆን ለራሱ እየባባ
    መስመሩ ሲጠፋው የመውጫው ቀዳዳ
    የውስጡ ባዶነት ሲሆንበት እዳ

   ጓደኛ ምን ይሰራል ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ወላጅ፣ … ወዘተረፈስ እኔ ስወለድ ብቻየን እንጅ ይህ ሁሉ ግሳንግስ አብሮኝ አልመጣ፡፡ የሰው ልጅ ይኖር ዘንድ የሚያስፈልገው እነዚህ ሁሉ ገተቶች ሳይሆኑ ገንዘቡና ገንዘቡ ብቻ ናቸው፡፡ ምንም ከነሌለው ሁሉ ይርቀዋል፡፡ ሁሉም ዝቅ አድርጎ ያየዋል፡፡ ራሱን ጥሎ ካገኘው ደግሞ እንዳይነሳ ለማድረግ እዚያው ይደፍቀዋል፡፡ ከበለጠው ደግሞ ጠልፎ ለመጣል መንገድ እያመቻቸ የራሱን ጥሎ የተሳካለትን ጠረን ሲያሸት ይውላል፡፡

እኔስ በደከምኩ ሰዓት ማን ሊያቃናኝ መጣ እኔ ራሴ በራሴ ተፍጨርጭሬ አይደለም የራሴን እንጻ የገነባሁት ፎቁስ ቆሞ እንዲታይ የሆነው በራሴ ጥረት አይደለምን ይለፈልፋል በሄደበት ሁሉ፡፡ ማንም ሰው ሊሰማው አይፈቅድም፡፡ ጆሮውን እየሰጠው ልቡን ይነፍገዋል፡፡ ዐይኑን አውሶ አእምሮውን ይነሳዋል፡፡ በአካል አብሮት ቆሞ በመንፈስ ይርቀዋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ለርሱ ምኑም አይደል፡፡ የሚከታተለው ኖረ አልኖረ፣ ተሰማ አልተሰማ፣ ታየ አልታየ … ምንም ደንታ የለው፤ ብቻ ግን ሁሌም ያወራል፡፡

ጎበዝ ተማሪ ነበር አሉ፤ ጓደኞቹ መተት አሰርተውበት ነው አሉ እንዲህ የሆነው፡፡ አይደለም! አንዲት ሴት ወዳው አስደግማበት ነው ይባላል፡፡ አይደልም! ይልቅስ አንዲት ቆንጆ ሴት አፍቅሮ ሲከተላት እሷ ደግሞ ሌላ ወንድ ይዘበት ነው እንዲህ አቅሉን የሳተውም ይባላል፡፡ ሴትና ሴታሴቶች ያናቡጉታል፡፡

ድንገት ከየት መጣ ያልተባለ ጎርናና የአዛውንት መሆኑ በውል ያልለየ ድምጽ የለ የለም! በቡተሊካ ምክኛት ታስሮ ወፌ ላላ ከተገረፈ በኋላ ነው አሉ እንዲህ የሆነው ይባላል፡፡ ሌላ ደግሞ ቁጣ ይሁን ለቅሶ ለመለያት ያዳገተ ድምጽ አይደለም አባየ! እናቱና ታላቅ ወንድሙ በአንድ ቀን በጥይት ሲገደሉ አጠገባቸው ሆኖ በማየቱ ደንግጦ ነው እንዲህ የሆነው ይባላል፡፡ ከሁሉም አቅጣጫ ግምት ይሠነዘራል፡፡ ማንም ዘንድ ግን እውነተኛው ምክንያት አልተገኘም፡፡ ምናልባትም በዛ ሰው ልብ እና አእምሮ ውስጥ ታሽጋ ተቀምጣ ሊሆን ይችላል፤ እስከመጨረሻውም ሳትገለጥ ልትቀር ትችላለች፡፡

ህይወት ኡደት ነች፡፡ የደረሱበትን አልፈው ያልደረሱት ተደርሶ ተመልሶ የመጀመሪያው ስፍራ ላይ የሚታረፍባት፡፡ እንደ ፕሮፌሰሩ የመሰላል ግጥም የረገጡትን አስጨብጣ የጨበጡትን የምታስረግጥ፡፡በምብርክክ አስሂዳ በመኪና ምታንፈላስስ፡፡

ጌታ ያድናል፡፡ ሁሉም ነገር በርሱ ነው፡፡… ቅብርጥሴ፣ ይሰብኩኛል፡፡ አሜን ብያቸው አልፋለሁ፡፡ 

 እኔ የማወራት የእርሷ ጆሮ ሲደርስ መልኩን እየሳተ እየተቀየረ፣ ከማፋቀር ይልቅ እኛን ከማዋደድ ጥል ፈጣሪ ኾነን እያጠራጠረ፡፡